አዋሽ ባንክ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት የብር 5 ሚሊየን ድጋፍ አድርጓል።
የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ ጸጋዬ ማሞ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት ተልዕኮዎችን ለማስፈጸም የአጋሮችን ድጋፍ በመጠየቅ ሃብት የማሰባሰብ ስራ መሰራቱን የገለፁ ሲሆን ባንኩ ላደረገው ድጋፍ በክልሉ መንግስት ስም በማመስገን በክልሉ ባንኩ ለሚሰራቸው ስራዎች የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የአዋሽ ባንክ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ዋና ዳይሬክተር ይርጋ ይገዙ በበኩላቸው የአዋሽ ባንክ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ክልላዊና ሀገራዊ ጥሪዎችን በመቀበል ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ለመነሻ የሚሆን የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ከማድረጉም በተጨማሪ በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
አዋሽ ባንክ ከምስረታው ጀምሮ የፋይናንስ አገልግሎቱን ተደራሽ ከማድረጉም ባሻገር ለማህበረሰቡ እገዛና ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡