አዋሽ ባንክ በአምቦ ከተማ አዲስ ህንፃ ሊገነባ ነው

በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች የራሱን ህንፃ በመገንባት የሚታወቀው አዋሽ ባንክ በአምቦ ከተማ ጠቅላላ የቦታው ስፋት 1,280 ካ.ሜትር ላይ የሚያርፍ እና ከምድር በታች ቤዝመንት ያለው ባለ ሰባት ወለል (G+7) አዲስ ዘመናዊ ህንፃ ለመገንባት የህንፃውን አርክቴክቸራል ዲዛይን ስራ አጠናቋል፡፡ ባንኩ የህንፃውን አርክቴክቸራል ዲዛይን ለማሰራት ባወጣው ጨረታ ተወዳድሮ ላሸነፈው አማካሪ ድርጅትም የእውቅና ሰርቲፍኬት እና የገንዘብ ሽልማት አበርክቷል::
ምንም እንኳን ከተወዳደሩት ድርጅቶች አንደኛ የወጣው በስራው ቢመረጥም በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችንም ለማበረታታት ሲባል አንደኛ ለወጣው የብር 125 ሺህ እንዲህም ሁለተኛ ለወጣው የብር 100 ሺህ የገንዘብ ሽልማትና የእውቅና ሰርቲፍኬት በባንኩ ተበርክቶላቸዋል፡፡ አዲሱ የአዋሽ ባንክ አምቦ ቅርንጫፍ ህንፃ ግንባታም በቅርቡ እንደሚጀመርና በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚውል የባንኩ ቺፍ ሆልሴል ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ ታደሰ ገመዳ ተናግረዋል፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Apr 25, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.8795 58.0171
GBP
67.5577 68.9089
EUR
60.7928 62.0087
AED
14.0132 14.2935
SAR
13.7240 13.9985
CHF
59.3920 60.5798

Exchange Rate
Close