አዋሽ ባንክ በብድር ላይ የሚከፈለውን የወለድ ምጣኔ ዝቅ እንዲል አደረገ::

አዋሽ ባንክ በብድር ላይ የሚከፈለውን የወለድ ምጣኔ ዝቅ እንዲል አደረገ::

አዋሽ ባንክ በብድር ላይ የሚከፈለውን የወለድ ምጣኔ ከ 0.5%-4.5% ዝቅ እንዲል አድርጉዋል፡፡ ባንኩ በብድር ላይ የሚከፈለውን የወለድ ምጣኔ ከ 0.5% – 4.5% ዝቅ እንዲል ያደረጉት ዋና ዋና ምክንያቶች፡-

1. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቦንድ ግዥ መመሪያን ማሻሻሉ አዋሽ ባንክ ለቦንድ ግዥ  የሚያውለውን ገንዘብ ለብድር በማዋል ትርፋማነቱን በአስተማማኝ ሁኔታ መቀጠል የሚያስችለው መሆኑ በጥናት በመረጋገገጡ፣

2. በብድር ላይ የሚከፈለው የወለድ ምጣኔ ዝቅ መደረጉ በአገራችን እየታየ ያለውን የዋጋ  ግሽበት ለማስተካከል የራሱ የሆነ በጎ ተጽእኖ ይኖረዋል ተብሎ ስለታመነ፣

በአጠቃላይ የወለድ ምጣኔ ማስተካከያው የአገራችንን የኢንቨስትመንት እና የንግድ እንቅስቃሴ በማበረታታት ለአገራችን የኢኮኖሚ መረጋጋት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ይታመናል፡፡

የአዋሽ ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቦንድ ግዥ እ.ኤ.አ ኦክቶበር፣ 2019 መጨረሻ ላይ ብር 12.4 ቢሊዮን ነበር፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Mar 28, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.6139 57.7462
GBP
68.2965 69.6624
EUR
61.3298 62.5564
AED
13.9500 14.2290
SAR
13.6595 13.9327
CHF
59.6955 60.8894

Exchange Rate
Close