ጋዜጣዊ መግለጫ

(መስከረም 15/2013 ዓ.ም አዲስ አበባ)፡  አዲሱ አመት የመጀመሪያ ሳምንት ላይ በሀገራችን በስፋት መነጋገሪያ ከሆኑት ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ በዋናነት መንግስት ፕሮጀክት ‘ኤክስ’ (X) የሚል ስያሜ በመስጠት በከፍተኛ ሚስጥርና ጥንቃቄ ሲያከናውን የቆየውንና መስከረም 04 ቀን 2013 ዓ.ም ይፋ የተደረገው የብር ኖቶች ቅየራ ተጠቃሽ ሲሆን አዋሽ ባንክም የብር ኖት ለውጡን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመርያ መሰረት የአዳዲሶቹ የብር ኖቶች ቅያሪ መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚገኙ ቅርንጫፎቹ በመጀመር የመጀመሪያው የግል ባንክ ሆኗል፡፡
በመሆኑም፡- ባንኩ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በሐረር፣ በሻሸመኔ፣ በጅማና በነቀምቴ ከተሞች ባሉት ስድስት ኢሹ ቅርንጫፎቹ በመታገዝ አገልግሎቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ በፍጥነት ሊያዳርስ የቻለ ሲሆን እንደ አዋሽ ባንክ ተጨባጭ ሁኔታ ዛሬ ላይ አዳዲሶቹን የብር ኖቶች በመላው ቅርንጫፎቹ የማዳረስ ስራ 99.4 በመቶ ተከናውኗል፡፡ይህም ማለት ባንኩ ካሉት 473 ቅርንጫፎቹ ውስጥ ለ470ዎቹ አዳርሷል ማለት ነው፡፡ እስከዚህ ሰዓት ድረስ አዳዲሶቹ የብር ኖቶች ያልደረሳቸው በምዕራብ ቀጠና ጽ/ቤት ስር የሚገኙ ሙጊ፣ ከማሺ እና ኖሌ ካባ ብቻ ሲሆኑ ለእነሱም ዛሬ ይደርሳቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ባሉት ቅርንጫፎቹ ከማሰራጨት ባሻገር ከብሔራዊ ባንክ የተረከበውን አዳዲስ የብር ኖቶችን ለሌሎች የግል ባንኮችም አሰራጭቷል፡፡ በዚህም መሰረት ከብሔራዊ ባንክ ከተረከበው 4 ቢሊዮን 072 ሚሊዮን 500ሺህ ብር ውስጥ 2ቢሊዮን 138 ሚሊዮን 975 ሺህ ብር አዳዲስ የብር ኖቶችን አሰራጭቷል፡፡

አዋሽ ባንክ በተለያዩ ጊዜያት በመንግስት ዕውቅናና ምስጋና የተቸረው ሲሆን ባለፈው በጀት ዓመት ብቻ ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር በመክፈል የዓመቱ ታማኝና ከፍተኛ ግብር ከፋይ በመባል በፕላቲኒየም ደረጃ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

አዋሽ ባንክ ምንም እንኳን ለትርፍ የተቋቋመ የግል ፋይናንስ ተቋም ቢሆንም አገራዊ ማህበራዊ ግዴታውን በመወጣትም በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው፡፡ መንግስት ለሚቀርፃቸው የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች በግንበር ቀደምትነት ይደግፋል ለአብነትም የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በቦንድ ግዥና በገንዘብ ልገሳ እየደገፈ ነው፡፡ በቅርቡም የመጀመሪያውን ምዕራፍ የውሃ ሙሌት በድል መጠናቀቅን በማስመልከትና ለቀሪው የግድቡ ግንባታ አለኝታነቱን ለመግለፅ በብር 25 ሚሊዮን የቦንድ ግዥ አከናውኗል፣ ለሸገር ማስዋብ ፕሮጀክትም የብር 15 ሚሊዮን የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ አሻራውን አኑሯል፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የአረንጓዴ አሻራ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ በጀት በመመደብ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናውኗል፣

የኮሮና ቫይሰረስ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም እና ለቅድመ ጥንቃቄ ስራ በብሔራዊ ደረጃ ለተቋቋመው የብሔራዊ የኮሮና መከላከል ኮሚቴ የብር 10 ሚሊን የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፤ በአገር አቀፍ ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተላለፈው የማዕድ ማጋራት ጥሪም ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ አደርጓል፡፡

በዘንድሮ ዓመት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ የተደረገውና በኦሮሚያ በወንጪ ሐይቅ፣ በአማራ በጎርጎራ እና በደቡብ ክልል በኮይሻ ለመስራት ለተቀረፀው የገበታ ለአገር ፕሮጀክትም ለእያንዳንዳቸው የብር 10 ሚሊዮን በድምሩ የብር 30 ሚሊዮን የገንዘብ ድጋፍ አድረጓል፡፡

ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቀርፆ ተግባራዊ ለሆነው ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁሶችን የማሟላት ስራን በሰፊው ደግፏል፤ ዘንድሮም ለተማሪዎች ምገባ ፕሮግራምና ለትምህርት ግብዓቶች ማሟያ የብር ሶስት ሚሊየን የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
አዋሽ ባንክ በዘርፉ ፈር ቀዳጅ እንደመሆኑ መጠን የአገሪቱ የፋይናንስ ህጎችን አክብሮና በየጊዜው በብሔራዊ ባንክ የሚወጡ መመሪያዎችን በአግባቡ በመተግበር ላለፉት 26 ዓመታት በስኬት ጎዳና ላይ ያለና በሁሉም የዘርፉ መመዘኛዎች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ መሪ የግል ባንክ ነው፡፡

Share
Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram

Apr 25, 2024 EXCHANGE Rate
Currency Buying Selling
USD
56.8795 58.0171
GBP
67.5577 68.9089
EUR
60.7928 62.0087
AED
14.0132 14.2935
SAR
13.7240 13.9985
CHF
59.3920 60.5798

Exchange Rate
Close