Open from November 12 -16, 2019
አዋሽ ባንክ በተለያዩ መርሃግብሮች 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው
Awash Bank and Amref Health Africa Signed a Partnership Agreement
Awash Bank, the leading private bank in Ethiopia and Amref Health Africa, the largest Africa based international non-governmental organization (NGO) signed today a long term partnership agreement to work jointly towards improving the health and well-being of Ethiopians, support progress towards Universal Health Coverage (UHC) and collaborate to narrow gender inequity gaps across Ethiopia.
As part of this long term partnership agreement and its first initiative working with Amref Health Africa, Awash Bank now provides financial support for the construction of 10 sanitation facilities to be implemented by Amref Health Africa in selected government schools in Addis Ababa. The project is expected to improve sustainable and equitable access to WASH for more than 20,000 school communities, and will be put into practice immediately up on the signing of the agreement document by both parties. This first intervention appears to be an important commitment to address the sanitation and hygiene problems of school children in their school setting; thereby contribute to the Sustainable Development Goals.
Following this partnership agreement signed today, Awash Bank and Amref Health Africa will also identify opportunities for long term strategic partnership and future impact investment projects.
Amref Health Africa, headquartered in Kenya, is the largest Africa based international non-governmental organisation (NGO) currently running programs in over 35 countries in Africa with lessons learnt over 60 years of engagement with governments, communities and partners to increase sustainable health access in Africa. Amref Health Africa also incorporates programme development, fundraising, partnership, advocacy, monitoring and evaluation, and has offices in Europe and North America as well as subsidiaries; Amref Flying Doctors, Amref Enterprises and the Amref International University.
With its Corporate Social Responsibility (CSR) program, Awash Bank, has been contributing a lot to public development programs for the last 25 years. Since its inception, the bank has been pledging millions of Birr to the vulnerable and marginalized sections of the society. The Bank will soon mark its silver jubilee in collaboration with its sister company – Awash Insurance with a serious of colorful events.
Awash Bank to construct new building at Bulbula
Awash Bank signed contractual agreement with Rama Construction plc to undertake the office building for its Bulbula Branch with a total cost of ETB 662,003,824.36.
The building will have 13 floor and expected to be completed within 36 months.
አዋሽ ባንክ ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከ7.5 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የትምህርት ቁሳቁሶችን አበረከተ..
አዋሽ ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አነሳሽነት በተጀመረው ‘ስጦታ ለአዲስ አበባዬ’ የበጎ አድራጎት ንቅናቄ መሰረት በመስተዳድሩ በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመንግስት ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ ተማሪዎች የተለያዩ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ለማሟላት በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ማህበራዊ ሃላፊነት ለመወጣት በማሰብ 659,584 የመማሪያ ደብተሮችን ከ7.5 ሚሊዮን ብር በላይ አውጥቶ በመግዛት ነሐሴ 10 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት በመገኘት ለከተማ መስተዳድሩ አበርክቷል፡፡ ባንኩን በመወከል ስጦታውን ያበረከቱት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታቦር ዋሚ እና የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ዮሐንስ መርጋ ሲሆኑ ከተማ አስተዳደሩን በመወከል ስጦታውን የተረከቡት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ናቸው፡፡
ምክትል ከንቲባው ስጦታውን በተረከቡበት ወቅት አዋሽ ባንክ ቀደም ሲልም በተለያዩ ዘርፎች ላይ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ መቆቱን በማውሳት ባንኩ ለሃገር ተረካቢ ተማሪዎች ላደረገው ተምሳሌታዊ የሆነ ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ሌሎች ተቋማትም መሰል ድጋፎችን በማድረግ ለዚህ የተቀደሰ ዓለማ ላለው ታሪካዊ ጥሪ በጎ ምላሽ በመስጠት ከከተማ መስተዳድሩ ጎን እንዲቆሙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ አዋሽ ባንክን በመወከል ስጦታውን ለክቡር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ያስረከቡት የባንኩ የዳይሬክሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታቦር ዋሚ በበኩላቸው አዋሽ ባንክ ለትርፍ የተቋቋመ ተቋም ቢሆንም ተቀዳሚ ተልዕኮው ግን ለማህብረሰቡ በተለይም ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ጉዳዮች ላይ በግንባር ቀደምነት በመገኘት የበኩሉን ጉልህ አሻራ ማሳረፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዚህ ‘ስጦታ ለአዲስ አበባዬ’ በተሰኘው መልካም አላማን አንግቦ ለተነሳው ግብ መሳካት ባንኩ የበኩሉን ለመወጣት ካለው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ የተበረከተው ደብተር በገንዘብ ሲተመን ከ7.5 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን የገለፁት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ፣ አዋሽ ባንክ በኮርፖሬት ማህበራዊ ኃላፊነት ፕሮግራሙ በየዓመቱ ከፍተኛ በጀት በመመደብ በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ ላሉት ማህበራዊ ግላጋሎት ሰጪ ለሆኑ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡
በሌላም በኩል አዋሽ ባንክ የማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ለተፈናቀሉ እና በድንገተኛ አደጋ ለተጐዱ እንዲሁም በፌደራል እና በክልል መንግሥት ደረጃ ለታቀዱ የዕድገት እና የልማት ኘሮጀክቶች በከፍተኛ ደረጃ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀው በቅርቡ በክቡር ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት ለተጀመረው የሸገር ማስዋብ ፕሮግራምም ባንኩ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን በማውሳት ይህንን መሰል ተግባር ለወደፊቱም አጠናክሮ በመቀጠል ህዝባዊ ወገንተኝነቱን በሁሉም መስክ እንደሚያረጋግጥም አስታውቀዋል፡፡
አዋሽ ባንክ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ቅርንጫፎችና ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆችን ሸለመ
አዋሽ ባንክ እ.ኤ.አ በ2018/19 የሂሳብ ዓመት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች እና ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች እውቅና እና ሽልማት ሰጠ፡፡ ባንኩ ሽልማቱን የሰጠው ሐምሌ 29 እና 30 2011 ዓ.ም ባካሄደው ዓመታዊ የስራ አመራሮች ስብሳባ መጨረሻ ላይ ሲሆን ተሸላሚዎቹ ቅርንጫፎችም በሂሳብ ዓመቱ ባስመዘገቡት ከፍተኛ ትርፍና በሐዋላ አገልግሎት በርካታ ደንበኞችን በማስተናገድ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት የተመረጡ ናቸው፡፡
ቅርንጫፎቹ ካስመዘገቡት አመርቂ ውጤት ጀርባ ቅርንጫፎቹን በቅርበት በማገዝ፣ በመከታተል፣ አቅጣጫ በመጠቆም፣ አዳዲስ ደንበኞችን በመመልመልና ነባር ደንበኞችን በመጎብኘት፣ መልካም ተሞክሮዎችን በማጋራት አቅም ግንባታው ላይ በመስራትና የተለያዩ ድጋፎችን ያደረጉ የቀጠና ስራአስኪያጆችም በዚሁ ፕሮግራም ላይ ምስጋናና ሽልማት ተችረዋል፡፡
ተሸላሚ ቅርንጫፎቹ እንዳስመዘገቡት ውጤት ዋንጫና የምስክር ወረቀት የተሸለሙ ሲሆን የተሸለሚ ቅርንጫፎችና ቀጠናዎች ስራ አስኪያጆችም የአንድ አንድ ወር ደመወዝ ተጨማሪ ቦነስ እና የአንድ አንድ እርከን ተጨማሪ የደመወዝ ጭማሪ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡት 23 ቅርንጫፍ አራት ቀጠና ስራ አስኪያጆችን ለማበረታታት ለአጭር ጊዜ ስልጠና ወደ ውጭ አገር እንደሚላኩም የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው በፕሮግራሙ መዝጊያ ላይ አሳውቀዋል፡፡