ለማህበረሰብ መቆርቆርን አንኳር እሴቱ ያደረገው አዋሽ ባንክ በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ በከባድ ዝናብ ቤታቸው ለወደመባቸው አርሶ አደሮች የቆርቆሮ ድጋፍ አድርጓል።
በሰሜን ሜጫ ወረዳ ሰኔ 4 እና ሰኔ 9/2014 ዓ.ም በጣለው በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በ9 ቀበሌ 2ሺህ 631 አርሶ አደሮች የመኖሪያ ቤት፣ አትክልትና ፍራፍሬ ሌሎች ሰብሎችም ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የተናገሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አንተነህ ወንዱ፣ አዋሽ ባንክ 1ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በሚሆን ወጪ ለተጎጂ አርሶ አደሮች ድጋፍ በማድረጉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
አዋሽ ባንክ ከምስረታው ጀምሮ የፋይናንስ አገልግሎቱን ተደራሽ ከማድረጉም ባሻገር በማንኛውም ወቅት ድንገተኛ አደጋዎች በሚያጋጥሙ ጊዜም ከማህበረሰቡ ጎን መቆሙን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዋሽ ባንክ ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሠረት አምበሉ በድጋፍ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ገልፀዋል፡፡
Featured
ታላቅ የምስራች አዳዲስ የስራ ፈጠራ ሀሳብ ላላችሁ በሙሉ
ታታሪዎቹ የተሰኘው የአዋሽ ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር ለመሳተፍ የማመልከቻ ጊዜ ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ አዳዲስ እና ችግር ፈቺ የሆኑ የስራ ሀሳቦች ያላችሁ ሁሉም የሀገራችን ዜጎች የፈጠራ ሃሣብ የማመልከቻ ቅጽ ከአዋሽ ባንክ ድህረ-ገፅ፣ ፌስ ቡክ እና የቴሌግራም ገጾች እንዲሁም የባንኩ ቅርንጫፎች በመውሰድ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን በታላቅ አክብሮት እናሳውቃለን፡፡
አዋሽ ባንክ!
ታላቅ የምስራች አዳዲስ የስራ ፈጠራ ሀሳብ ላላችሁ በሙሉ::Baankiin Awaash dorgomii Kalaqa hojii yeroo gabaabaa keessatti jalqabuuf.
አዋሽ ባንክ የስራ ፈጠራ ወድድር በቅርቡ ሊጀምር ነዉ:: የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው የውድድሩ ተሳታፊዎች የሙያዊ ክህሎት ስልጠና እንዲሁም በየደረጃው የገንዘብ ሽልማት የሚያገኙ ሲሆን ከ1ኛ እሰከ 5ኛ የሚወጡ የመጨረሻዎቹ የውደድሩ አሸናፊዎችም ከብር 200 ሺህ እስከ አንድ ሚሊዮን የገንዘብ ሽልማትና የፈጠራ ሀሳባቸውን ተግባራዊ የሚያደርጉበት እስከ ብር አምስት ሚሊዮን የሚደርስ ከዋስትና ነፃ የብድር አገልግሎት ይመቻችላቸዋል፡፡
Dorgommichi lammiilee kalaqa hojii qabaniifi hanqinnii ogummaa fi faayinaansii gufuu itti ta’eef leenjii gahumsa ogummaafi ijaarsa dandeettii akkasumas dhiyeessii faayinaasiitiif haala ni mijeessa.
Dorgommii kanarratti lammiileen dandeettii waa uumuu qaban hundi ni dorgonu, kanneen 1ffaa hanga 5ffaa bahanimmoo birrii kuma 200 hanga miiliyoona tokkoo ni badhaafamu, utuu homaa hin qabsiisiin tajaajili liqii hanga birrii miiyoona shaniis akka pirojektii ittiin dorgomanii mo’atan hojiirra oolchaniif ni mijaa’aaf.
አዋሽ ባንክ የስራ እድል ፈጠራን የሚያበረታታ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ:: Baankiin Awaash Pirojektii Kalaqa Hojii jajjabeessu ifoomse.
አዋሽ ባንክ በሀገራችን የስራ ፈጠራን በማበረታታት የስራ አጥነት ችግርን ሊፈታ የሚችል “ታታሪዎቹ” የተሰኘ ፕሮጀክት ቀርጾ ወደ ተግባር መግባቱን በዛሬው እለት የስራና ክህሎት ምኒስቴር ምኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈርሃት ካሚል በተገኙበት ይፋ አድርጓል፡ፕሮጀክቱ ስራ ፈጠራን በማበረታታት፣ ክህሎት ላላቸው ስራ ፈጣሪዎች የቢዝነስ ሙያ ስልጠና እና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ስራ አጥነትን ለመቅረፍ ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።
Baankiin Awaash Pirojektii kalaqa hojii jajjabeessu kan sadarkaa biyyaalessaatti hojiirra oolu guyyaa har’aa Bakka Ministirri Ministeera Hojii fi kalaqaa Aadde Mufariyaat Kaamil argamanitti ifoomsee jira.
አዋሽ ባንክ የኢፍጣር መርሐ-ግብር አካሄደ።
አዋሽ ባንክ የታላቁ የረመዳን ወርን በማስመልከት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም ምኞቱን ለመግለጽና ለደንበኞቹ ያለውን አጋርነት ለማረጋገጥ በማሰብ በ ቀን 11,2014 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል የጋራ የኢፍጣር ሥነ-ሥርዓት ያካሄደ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ባንኩ የሸሪአ መርሆችን መሰረት አድርጎ በማቅረብ ላይ በሚገኘው ‘’አዋሽ ኢኽላስ’’ የተሟላ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቶች በተጨማሪ ኢጃራ ፋይናንሲንግ፣ ቃርዱል ሀሰን ፋይናንሲንግ እንዲሁም አል- ከይር ዋድያ (የተቀማጭ ሂሳብ) የተሰኙ አዳዲስ ፕሮዳክቶችን በይፋ አስጀምሯል፡፡
በመርሐ-ግብሩ ላይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራውን ጨምሮ ፣ የአዋሽ ባንክ የሸሪዓ አማካሪዎች ፣ የባንኩ የሥራ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ ባንኩ በሸሪዓ መርሆች ላይ የተመሰረተውን የአዋሽ ኢኽላስ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ዓይነቶችና ተደራሽነት ለማስፋት ጠንክሮ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! Baga Gammaddan! Baga Gammanne!
አዋሽ ባንክ ከዓለም ምርጥ ባንኮች ውስጥ አንዱ ሆኖ ተመረጠ፡፡ ግሎባል ፋይናንስ ለ29ኛ ጊዜ ዓመታዊ የዓለም እና የየአገሮች ምርጥ ባንኮችን ምርጫ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚሁ መሠረት ከአፍሪካ አህጉር 36 ባንኮች የተመረጡ ሲሆን የአፍሪካ አንደኛ ምርጥ ባንክ ብሎ የተሰየመው የደቡብ አፍሪካው ስታንዳርድ ባንክ ሲሆን ከኢትዮጵያ ደግሞ አዋሽ ባንክ በብቸኝነት ተመርጧል፡፡ የምርጫው ዋና ዋና መስፈርቶች ባንኮቹ ያስመዘገቡት ውጤት በተለይም ትርፋማነት’፣የሀብት ዕድገትና ተደራሽነት’፣ለደንበኞቻቸው ያሳዩት ቅን አገልግሎት እና ለወደፊት ስኬት የጣሉት አስተማማኝ መሠረት መሆኑን ተቋሙ ይፋ አድርጓል፡፡
በምርጫው አሸናፊ ለሆኑ ባንኮች ዕውቅና ሽልማት የሚሰጠው እ.ኤ.አ. በኦክቶበር 2022 የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ (WB) በአሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ በሚያደርጉት የጋራ ጉባዔ ላይ እንደሆነም ታውቋል፡፡
Baankiin Awaash Baankilee Filatamoo adduunyaa keessaa tokko ta’uun filatamee jira. Dhaabbatni Giloobaal Faayinaans jedhamu yeroo 29ffaaf Baankilee filatamoo adduunyaa kanaa ifa godhee jira. Kanaan walqabatee Ardii Afriikaa irraa Baankiiwwan 36 kan filataman yoo ta’u, tokkoffaa ta’uun kan filatame Afriikaa kibbaa irraa Baankii Istaandaard yeroo ta’u, Itiyoophiyaa irraa ammo Baankiin Awaash filatamee jira. Ulaagaaleen filannoo kanaa raawwii hojii baankotaa keessaayyuu bu’aa galmeessisan, guddina qabeenya waliigalaa, qaqqabamummaa ykn hawaasatti dhiyeenyaan tajaajiluu, akkasumas tajaajila gaarii maamiloota isaanif kennuu fi guddina fuuldura isaanitiif bu’uura cimaa kaa’uudha.
Badhaasni fi beekkamtiin Ijifattoota filannoo kana kan kennamu A.L.A Onkoloolessa bara 2022Yaa’ii waliinii Dhaabbanni Maallaqa Adduunya (IMF) fi Baankiin Adduunya (WB) biyya Ameerikaa ,Magaalaa Waashingitan Diisiitti gaggeessan irratti kan kennamu ta’uun beekameera.