በባንካችን ከብር 200 ጀምሮ በመቆጠብ የውጭ ሀገር ገንዘብ በመቀበልና በመመንዘር የሎተሪ ዕጣ አሸናፊ ይሁኑ!
ከሚያዚያ 05/2014 ዓ.ም ጀምሮ በ10ኛዉ ዙር “በአዋሽ ይቆጥቡ ፤ ይቀበሉ፤ይሸለሙ!” መርሀ ግብር ዕድለኛ ደንበኞች የሚንበሸበሹባቸዉን በርካታ ሽልማቶች አዘጋጅተናል፡፡
News
አዋሽ ባንክ የኢፍጣር መርሐ-ግብር አካሄደ።
አዋሽ ባንክ የታላቁ የረመዳን ወርን በማስመልከት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም ምኞቱን ለመግለጽና ለደንበኞቹ ያለውን አጋርነት ለማረጋገጥ በማሰብ በ ቀን 11,2014 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል የጋራ የኢፍጣር ሥነ-ሥርዓት ያካሄደ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ባንኩ የሸሪአ መርሆችን መሰረት አድርጎ በማቅረብ ላይ በሚገኘው ‘’አዋሽ ኢኽላስ’’ የተሟላ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቶች በተጨማሪ ኢጃራ ፋይናንሲንግ፣ ቃርዱል ሀሰን ፋይናንሲንግ እንዲሁም አል- ከይር ዋድያ (የተቀማጭ ሂሳብ) የተሰኙ አዳዲስ ፕሮዳክቶችን በይፋ አስጀምሯል፡፡
በመርሐ-ግብሩ ላይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራውን ጨምሮ ፣ የአዋሽ ባንክ የሸሪዓ አማካሪዎች ፣ የባንኩ የሥራ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ ባንኩ በሸሪዓ መርሆች ላይ የተመሰረተውን የአዋሽ ኢኽላስ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ዓይነቶችና ተደራሽነት ለማስፋት ጠንክሮ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! Baga Gammaddan! Baga Gammanne!
አዋሽ ባንክ ከዓለም ምርጥ ባንኮች ውስጥ አንዱ ሆኖ ተመረጠ፡፡ ግሎባል ፋይናንስ ለ29ኛ ጊዜ ዓመታዊ የዓለም እና የየአገሮች ምርጥ ባንኮችን ምርጫ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚሁ መሠረት ከአፍሪካ አህጉር 36 ባንኮች የተመረጡ ሲሆን የአፍሪካ አንደኛ ምርጥ ባንክ ብሎ የተሰየመው የደቡብ አፍሪካው ስታንዳርድ ባንክ ሲሆን ከኢትዮጵያ ደግሞ አዋሽ ባንክ በብቸኝነት ተመርጧል፡፡ የምርጫው ዋና ዋና መስፈርቶች ባንኮቹ ያስመዘገቡት ውጤት በተለይም ትርፋማነት’፣የሀብት ዕድገትና ተደራሽነት’፣ለደንበኞቻቸው ያሳዩት ቅን አገልግሎት እና ለወደፊት ስኬት የጣሉት አስተማማኝ መሠረት መሆኑን ተቋሙ ይፋ አድርጓል፡፡
በምርጫው አሸናፊ ለሆኑ ባንኮች ዕውቅና ሽልማት የሚሰጠው እ.ኤ.አ. በኦክቶበር 2022 የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ (WB) በአሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ በሚያደርጉት የጋራ ጉባዔ ላይ እንደሆነም ታውቋል፡፡
Baankiin Awaash Baankilee Filatamoo adduunyaa keessaa tokko ta’uun filatamee jira. Dhaabbatni Giloobaal Faayinaans jedhamu yeroo 29ffaaf Baankilee filatamoo adduunyaa kanaa ifa godhee jira. Kanaan walqabatee Ardii Afriikaa irraa Baankiiwwan 36 kan filataman yoo ta’u, tokkoffaa ta’uun kan filatame Afriikaa kibbaa irraa Baankii Istaandaard yeroo ta’u, Itiyoophiyaa irraa ammo Baankiin Awaash filatamee jira. Ulaagaaleen filannoo kanaa raawwii hojii baankotaa keessaayyuu bu’aa galmeessisan, guddina qabeenya waliigalaa, qaqqabamummaa ykn hawaasatti dhiyeenyaan tajaajiluu, akkasumas tajaajila gaarii maamiloota isaanif kennuu fi guddina fuuldura isaanitiif bu’uura cimaa kaa’uudha.
Badhaasni fi beekkamtiin Ijifattoota filannoo kana kan kennamu A.L.A Onkoloolessa bara 2022Yaa’ii waliinii Dhaabbanni Maallaqa Adduunya (IMF) fi Baankiin Adduunya (WB) biyya Ameerikaa ,Magaalaa Waashingitan Diisiitti gaggeessan irratti kan kennamu ta’uun beekameera.
አዋሽ ባንክ “በአዋሽ ይቆጥቡ ይቀበሉ ይሸለሙ” አሸናፊ ለሆኑ እድለኞች ያዘጋጀዉን ሽልማት አስረከበ
አዋሽ ባንክ ከግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም አስከ ጥር 11 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ሲያካሂድ የነበረውን የ9ኛው ዙር “በአዋሽ ይቆጥቡ ይቀበሉ ይሸለሙ” የሎተሪ መርሐ ግብር አሸናፊ ለሆኑ እድለኞች ያዘጋጀዉን ሽልማት አስረከበ፡፡
ለዘጠነኛው ዙር መርሐ ግብር የተዘጋጁት የሽልማት ዓይነቶች በአምስት ደረጃዎች የተከፋፈሉ ሲሆን ለአንደኛው ዕጣ የተዘጋጀው የሽልማት ዓይነት አንድ አይሱዙ ዘመናዊ የጭነት መኪና የሎተሪ ቁጥር 00027805864 የያዙት አቶ ሀብታሙ ወልዴ ፋንታሁን በጅማ ከተማ ጅሬን ቅርንጫፍ የባንክ አገልግሎት ባገኙበት ወቅት በተሰጣቸው የሎተሪ ዕጣ ቁጥር አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ለ2ኛ እጣ የተዘጋጀው ኪያ ፒካንቶ የቤት አውቶሞቢል የሎተሪ ቁጥር 00027414628 የያዙት አቶ በላቸው ስሜ አዱኛ ከገርባ ጉራቻ ከተማ ከገርባ ጉራቻ ቅርንጫፍ የደረሳቸው ሲሆን ለሶስተኛ ዕጣ (አስር ዕጣዎች) እያንዳንዳቸው ዘመናዊ ላፕቶፖች፣ ለአራተኛ ዕጣ (ሰላሳ ዕጣዎች) እያንዳንዳቸው 32 ኢንች ኤልኢዲ ቴሌቪዥኖች እንዲሁም ለአምስተኛ እጣ (ሀምሳ ዕጣዎች) እያንዳንዳቸው ስማርት የሞባይል ስልክ ቀፎዎችን ዕጣ ለወጣላቸው ለዕድለኞች ሽልማታቸውን አስረክቧል፡፡
በሽልማት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ለሎተሪ ዕጣ አሸናፊዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ እንደገለፁት ባንኩ ያዘጋጀው የሎተሪ መርሐ ግብር የማህበረሰቡን የቁጠባ ባህል በማሳደግ የተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ግንዛቤን ከመፍጠሩም ባሻገር ለአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆነውን የውጭ ምንዛሪ ፍሰት በሕጋዊ መንገድ እንዲመጣ በማድረግ የሚገኘውም የውጭ ምንዛሪ ለአገራችን ልማትና ዕድገት እንዲውል ለማስቻል የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ረገድ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ለመርሐ ግብሩ መሳካት ያልተቆጠበ ድጋፍ ላደረጉት የመንግስት፣ የግል ድርጅቶችና ግለሰቦችን ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
አዋሽ ባንክ ከብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በትብብር ለመስራት ተፈራረመ
አዋሽ ባንክ ከብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ። የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል ሲሆኑ በስምምነቱም ከመታወቂያ፣ ከመንጃ ፍቃድና ከባንክ እንዲሁም ከተለያዩ አገልግሎቶች ጋር በመተሳሰር ደንበኛው በቀላሉ ማንነቱ ተለይቶ አገልግሎት ማግኘት ከማስቻሉም ባሻገር ብሔራዊ መታወቂያው በሚሰጠው ልዩ ቁጥር አማካኝነት ግለሰቦችን ለመለየት እና በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚደረግን ማጭበርበር በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡
አዋሽ ባንክ የደንበኞች ሳምንትን በማክበር ላይ ይገኛል
አዋሽ ባንክ ‘’ለላቀ የደንበኞች እርካታ እንተጋለን’’ በሚል መሪ ቃል በሁሉም ቅርንጫፎቹ ውስጥ ከመጋቢት 06 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ በዓይነቱ ለየት ያለ የደንበኞች ሳምንት ቀንን እያከበረ ይገኛል፡፡ በደንበኞች ሳምንት የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው በቅርንጫፎች ላይ በመገኘት ለተለያዩ ደንበኞች የባንክ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡